ምንጭ፡-የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ
መግቢያ:
ወጣትነት ከሕፃንነት ወደ ዐዋቂነት
በሚደረገው ሽግግር ወቅት አንድን ሰው ለዐዋቂነት የሚያሸጋግሩ ስነልቦናዊ፣ አካላዊ፣ ማህበራዊና አዕምሮአዊ ለውጦች
የሚከናዎኑበት ጊዜ ነው፡፡ በወጣትነት ዘመን ከውስጣዊ ፈተና በተጨማሪ ውጫዊ ፈተና የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አለው፡፡ የተሻለ
የዐዋቂነት ሕይወት ለመምራት አንድ ወጣት እነዚህን ፈተናዎች በአሸናፊነት መወጣት አለበት፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን በዚህ ወሳኝ
ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራት እሙን ነው፡፡ በዚህ መልኩ ልጆቿን ኮትኩታ ባሉበት ፈታኝ ዘመን ፈተናውን ተቋቁመው
ማለፍ እንዲችሉ ማገዝ ከቻለች ለመንፈሳዊ ክብር ልታበቃቸው ትችላለች፡፡ በምላሹም ከወጣቶች የሚጠበቀውን መጠነ-ሰፊ አገልግሎት
ማግኘት ይቻላል፡፡
ወጣትነት
"ወጣት ማለት በሰው ልጅ ሥነ
ሕይወታዊ ምዕራፍ አንድን የእድሜ ክልል የሚወክል እና የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ሥነ-ልቦናዊ፣ ማሕበራዊ አቋምና ደረጃ ያለው
ነው፡፡ " ማኅበረሰቦች /ሀገራት/ የየራሳቸው ከሆኑ ማኅበራዊ፣ ባሕላዊና ሌሎችም እሴቶች ጋር በተያያዘ ወጣት የሚለውን
የዕድሜ ክልል ለያይተውት እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ፡ የዓለምጤናድርጅት "Adolescent" ማለትከ10-19 ዓመት
ዕድሜ ውስጥ የሚገኘውን የሕብረተሰብ ክፍል የሚወክል ሲሆን "Young peo¬ple" ማለትደግሞከ15-24 ዓመት
ድረስ ያለውን ይወክላል በማለት አስቀምጧል (Hand book of pediatrics AIDS , 187)፡፡ ወጣቶችን በተመለከተ
የተዘጋጁ የተለያዩ የሀገር ውስጥ ጽሁፎች በኢትዮጵያም ቢሆን ቃሉ የሆነ የዕድሜ ክልልን የሚወክል አድርገው ቢያቀርቡም ቁርጥ
ያለ ነገር ለማግኘት ግን አዳጋችነው፡፡ ለምሳሌ፡- ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊስ (National Youth Policy) ወጣትነትን
ከ15- 19 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ሲገድበው ከ2ዐዐ6 -2ዐ15 ድረስ እንዲያገለግል ተደርጎ የተዘጋጀው የወጣቶች
የሥነ-ተዋልዶ ትግበራዊ ስልት ዶኩሜንት (Ado-lecent & Youth Reproductive Health Strategy)
የዕድሜ ክልሉን ሰፋ 1ዐ- 24 ዓመት እንደ ሚያጠቃልል ይጠቁማል፡፡