ትላንት በተደረገው የሴቶች
5000 ሜትር ርቀት ኢትዮጵያ ድል የቀናት ሲሆን በውጤቱም መሠረት ደፋር አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ ጥሩነሽ ዲባባ ከተፍኛ የቡድን ስራ በመስራት ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ ማግኝት ችላለች፡፡
መሠረት ደፋር ማሸነፏን
ስታውቅ በከፍተኛ ደስታ ሆና በማልቀስ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ምስል በመያዝ እንባዋን መቆጣጠር እስከሚያቅጣት
ድረስ ብርታቷ ድንግል መሆኗን ያሳየችበት ታላቅ የሩጫ መድረክ ሆኖ አምሽቷል፡፡
No comments:
Post a Comment