ከህይወት ታሪካቸው ስንጀምር አንዳንዶች የአባታቸው ስም ደስታ ተገኝ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ገብረ ማርያም ነው ይላሉ። ምናልባት አንዱ የአለም ሌላው ደግሞ የክርስትና ስማቸው ሊሆን ይችላል። የተወለዱት በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በድሮው የደብረታቦር አውራጃ ፎገራ ወረዳ፤ ናብጋ ጊዮርጊስ በተባለው ቦታ በ1814 ዓ.ም ነው። የመጀመርያ ትምህርታቸውን በአካባቢው ከቀሰሙ በኃላ ወደ ጎጃም ተሻግረው ቅኔን ተቀኙ። ከዚያም ወደ ጎንደር ከተማ ተመልሰው ከመምሕር ወደ አብ ወልደ ማርያም ጽዋትወ ዜማ፤ ከባሕታዊ ገብረ አምላክ አቋቋም፤ ከዐቃቤ ስብሃት ገብረ መድሕን ትርጓሜ መጽሐፍትን እንዲሁም ድጓን ተምረዋል። በዚህ የሰፋ እውቀታቸው የተነሣ በ26 ዓመታቸው ጎንደር ሊቀካህናትነት ተሾመው ነበር። በዚህም ሹመት ለሰባት ዓመት ማገልገላቸው ይነገራል። በፍትሐ ነገሥት ሊቅነታቸው ደግሞ በዳኝነት እየተሰየሙ አገልግለዋል። አለቃ ገብረ ሐና ጨዋታ አዋቂነታቸው እየታወቀ የመጣው በዚህ ወቅት ነበር። በዚህም እውቀታቸው የትንሹ ዓሊ አጫዋች ሆኑ። አጼ ቴዎድሮስ ሥልጣኑን ሲይዙ አለቃን በቤተ መንግሥት አገኟቸው። አለቃ የቤተ መንግሥቱን ሰዎች በቀልዳቸው ሸንቆጥ ስለሚያደርጉ መስማማት አልቻሉም ነበር። እንዲያውም ዐጼ ቴዎድሮስ «ገብረ ሐና ፍትሐ ነገስቱን ጻፍ፤ ፍርድ ስጥ .. ገንዘብ ያውልህ፤ ቀልድህን ግን ተወኝ።» ሲሉ ተናግረዋቸው ነበር ይባላል። አለቃ ግን አላቆሙም።
Showing posts with label ታሪክ. Show all posts
Showing posts with label ታሪክ. Show all posts
Monday, April 30, 2012
Saturday, April 28, 2012
ግርማዊት ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ
ቅዳሜ ሚያዝያ ፳፪ ቀን ፲፰፻፷፰ ዓ.ም ከሸዋ ንጉሥ ምኒልክና ከወረኢሉ ተወላጅ ከወይዘሮ አብቺው በእነዋሪ ከተማ ተወለዱ።ሐምሌ ፲፩ ቀን ሰኞ ሥርዓተ ጥምቀት ተፈጽሞላቸው፣ የክርስትና ስማቸው አስካለ ማርያም ተባለ። ግርማዊት ንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ ለዳግማዊ ምኒልክ ሦስተኛ ልጅ ሲሆኑ ከልጅ ኢያሱ ቀጥለው መኳንንትና ሕዝቡ መክሮና ዘክሮ በምርጫ በኢትዮጵያ ዙፋን ላይ የተቀመጡ ብቸኛዋ ንግሥት ናቸው።
አባታቸው የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ (በኋላ ዳግማዊ ዐፄ) ዘውዲቱ የስድስት ዓመት ሕጻን እንደነበሩ ለአሥራ ሁለት ዓመቱ የዐፄ ዮሐንስ ልጅ ለአርአያ ሥላሴ ዳሩዋቸው። ጋብቻቸውም ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፰፻፸፭ ዓ.ም. በተክሊልና በቁርባን ተፈጸመ፡ የሠርጉም ማማርና የሽልማቱ ብዛት ሊነገር አይቻልም። ልጅ ኢያሱ መስከረም ፲፯ ቀን ፲፱፻፱ዓ.ም ከስልጣን ሲወርዱ፤ መኳንንቱና ሕዝቡ መክሮና ዘክሮ በምርጫ ወይዘሮ ዘውዲቱን ግርማዊት ንግሥተ ነገሥት፤ ራስ ተፈሪ መኮንንን አልጋ ወራሽ እና ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ እንዲሆኑ ወስነው መስከረም ፳፩ ቀን "ግርማዊት ዘውዲቱ፣ ንግሥተ ነገሥት ዘኢትዮጵያ" ተብለው ነገሡ። በመኳንንቱም ምክር መሠረት ጳጳሱና እጨጌ ወልደጊዮርጊስ "ኢያሱን የተከተልክ፣ ያነገሥናትን ዘውዲቱንና ራስ ተፈሪን የከዳህ፣ ውግዝ ከመአርዮስ" እያሉ በአዋጅ አወገዙ፡:
Subscribe to:
Posts (Atom)